ኢየሱስ ፡ በሚመራኝ ፡ መንገድ (Eyesus Bemimeragn Menged)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ በሚመራኝ ፡ መንገድ
ምንድር ፡ ያስጠይቀኛል?
ምሕረቱንም ፡ ይሰጠኛል
ሁልጊዜም ፡ ይመራኛል
ሰላሙን ፡ ያካፍለኛል
አምኜ ፡ እንድኖርበት
ከሚመጣብኝም ፡ ሁሉ
ኢየሱስ ፡ ይጠብቀኛል (፪x)

ኢየሱስ ፡ የሚመራኝ ፡ መንገድ
እጅጉን ፡ ደስ ፡ ያሰኛል
ፀጋውንም ፡ ይሰጠኛል
ሕያው ፡ ምግብ ፡ ይሰጠኛል
ከድካሜ ፡ እንዲያጸናኝ
ነፍሴም ፡ እንዳትጸማ
መንፈሱም ፡ ይፈልቅልኛል
በደስታም ፡ ያጠጣኛል (፪x)