ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ድኜ (Eyesus Bante Degnie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ድኜ
ገንዘብህም ፡ ሁኜ
በአንተ ፡ ጻድቅ ፡ ነኝ
ግን ፡ በዓለም ፡ ነገር
ልቤ ፡ እንዳይታሰር
አንተ ፡ ጠብቀኝ

ክፉው ፡ ጠላቴ
ወጥመድ ፡ ለጥፋቴ
ዘርግቶብኛል
በእኔ ፡ ሲቀናብኝ
ሃብቴን ፡ ሊነጥቅብኝ
ሠርክ ፡ ይሸምቃል

ስለዚህ ፡ ወደኛ
አንተ ፡ ቸር ፡ እረኛ
ናና ፡ ጠብቀን
ታናሽ ፡ መንጋህንም
ጋርድ ፡ አድነንም
ተንከባከበን