እውነተኞች ፡ ስንሆን (Ewunetegnoch Sinihon)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ስለ ፡ ጌታ ፡ ማዳን ፡ የምንመሰክረው
በዕውነት ፡ ቃልና ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ነው
ይህ ፡ ሲሆን ፡ በዕምነት ፡ ስደት ፡ የማይቀር ፡ ነው
ሆኖም ፡ ጌታ ፡ ይክበር ፡ ምልክታችን ፡ ነው

አዝ ፣
እውነተኞች ፡ ስንሆን ፡ አሳቾች ፡ ተብለን
ዝነኞች ፡ ስንሆን ፡ እንዳልታወቅን ፡ ሆነን
ሞተዋል ፡ ስንባል ፡ በሕይወት ፡ እንኖራለን
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ በጌታ ፡ ኃይል ፡ አለን

በችግር ፡ በጭንቀት ፡ በወኅኒ ፡ በሁከት
በድካም ፡ ላይ ፡ ድካም ፡ ዕንቅልፍን ፡ በማጣት
ታርዘን ፡ ስንራብ ፡ የምንታገሠው
ኃይልን ፡ በሚሰጠን ፡ በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝ ፣
እውነተኞች ፡ ስንሆን ፡ አሳቾች ፡ ተብለን
ዝነኞች ፡ ስንሆን ፡ እንዳልታወቅን ፡ ሆነን
ሞተዋል ፡ ስንባል ፡ በሕይወት ፡ እንኖራለን
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ በጌታ ፡ ኃይል ፡ አለን

የምንዋጋበት ፡ መከላከያችን
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ነው ፡ ዋናው ፡ መሣሪያችን
መለኮታዊ ፡ ኃይል ፡ አብዝቶ ፡ የሰጠን
የጌታችን ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን

አዝ ፣
እውነተኞች ፡ ስንሆን ፡ አሳቾች ፡ ተብለን
ዝነኞች ፡ ስንሆን ፡ እንዳልታወቅን ፡ ሆነን
ሞተዋል ፡ ስንባል ፡ በሕይወት ፡ እንኖራለን
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ በጌታ ፡ ኃይል ፡ አለን