እወድሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ (Ewedehalehu Eyesus Hoy)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እወድሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ወደ ፡ እኔ ፡ ና ፡ ከእኔም ፡ ዘንድ ፡ ቆይ
ከእኔም ፡ ተባበርልኝ
በዓለም ፡ ሁሉ ፡ ፈተና
ሥቃይም ፡ ብዙ ፡ አለና
አንተ ፡ ሰላም ፡ ሁንልኝ
ነፍሴም ፡ ሥጋዬም ፡ በሚመር
ሥቃይ ፡ ቢያልቅም ፡ ይህ ፡ ሳይቀር
ለልቤ ፡ ተስፋ ፡ ሰጠኸኝ
አደራህን ፡ ተቀበልኸኝ
ኦ ፡ ኢየሱስ ፤ ኦ ፡ መድኃኒቴ
መድኃኒቴ
አንተ ፡ ነህ ፡ መጸናናቴ

ምድራዊ ፡ ድንኳኔ ፡ ሲፈርስ
ወደ ፡ አንተ ፡ ነፍሴን ፡ ሊያደርስ
መልዓክህን ፡ ላክልኝ
ድኩም ፡ ሥጋዬም ፡ በሰላም
ይረፍ ፡ ከምድሩ ፡ ድካም
ድምጽህ ፡ እስኪያስነሣኝ
ስነሣም ፡ ልይህ ፡ ዓይን ፡ ለዓይን
ከአንተም ፡ ዘንድ ፡ አዲሱን ፡ ወይን
ልጠጣ ፡ በብፅዕናህም
ልወድሽ ፡ ላመስግንም
መድኃኒቴ ፡ ተቀበለኝ
ተቀበለኝ
ብኖር ፡ ብሞትም ፣ የአንተ ፡ ነኝ