ኢትዮጵያን ፡ ጐብኛት (Ethiopian Gobgnat)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ኢትዮጵያን ፡ ጐብኛት ፡ ተመልከታት
በቃል ፡ ኪዳንህ ፡ አስባት (፪X)

በዙፋንህ ፡ ያለኸው ፡ በከበረው ፡ ሥፍራ
በሰማየ ፡ ሰማያት ፡ በጽዮን ፡ ተራራ
የሆንከው ፡ ገናና ፡ ቅዱስ ፡ አምላካችን
ይህ ፡ ነው ፡ ልመናችን

አዝ፦ ኢትዮጵያን ፡ ጐብኛት ፡ ተመልከታት
በቃል ፡ ኪዳንህ ፡ አስባት (፪X)

እንደምትፀልይ ፡ እጆቿን ፡ አንስታ
ወደ ፡ አንተ ፡ ፈጣሪ ፡ ወደ ፡ ሕያው ፡ ጌታ
የገባኸውን ፡ ለእኛ ፡ አስብ ፡ ኪዳንህን
ስጠን ፡ በረከትህን

አዝ፦ ኢትዮጵያን ፡ ጐብኛት ፡ ተመልከታት
በቃል ፡ ኪዳንህ ፡ አስባት (፪X)

እናስቀምጣለን ፡ ሁሉንም ፡ በፊትህ
አምላክ ፡ በጐነትህ ፡ ብዙ ፡ ቸርነትህ
ሰላም ፡ ብልጽግና ፡ መለኮት ፡ ባርኮትህ
በብዙ ፡ ረድኤትህ

አዝ፦ ኢትዮጵያን ፡ ጐብኛት ፡ ተመልከታት
በቃል ፡ ኪዳንህ ፡ አስባት (፪X)