እስከዛሬ ፡ ድረስ ፡ ጠብቆኛል (Eskezarie Deres Tebeqognal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ጠብቆኛል
በክንፎቹ ፡ ጋርዶ ፡ ከልሎኛል
የዘለዓለም ፡ ክንዱን ፡ ጌታን ፡ ተንተርሼ
በሆነው ፡ ባልሆነው ፡ ቀረ ፡ መረበሼ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ምሥጋና
ያደረከው ፡ ተዐምራትህን ፡ በዝቷልና
በመሰንቆ ፡ በከበሮ ፡ በበገና
ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ምሥጋና

እባብና ፡ ጊንጡም ፡ አልደፈረኝ
አማሌቅ ፡ ፍልስጤም ፡ አላወከኝ
ዘንዶውን ፡ ረግጬ ፡ በድል ፡ አለፌአለሁና
ክብሬን ፡ አልጠብቅም ፡ እዘምራለሁ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ምሥጋና
ያደረከው ፡ ተዐምራትህን ፡ በዝቷልና
በመሰንቆ ፡ በከበሮ ፡ በበገና
ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ምሥጋና

በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ተጠግቼ
በመልካሙ ፡ እረኛ ፡ ተመርቼ
ብዙ ፡ ለምለም ፡ ስፍራ ፡ በእርሱ ፡ አይቼአለሁ
ነገንም ፡ አልፈራም ፡ አምነዋለሁ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ምሥጋና
ያደረከው ፡ ተዐምራትህን ፡ በዝቷልና
በመሰንቆ ፡ በከበሮ ፡ በበገና
ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ምሥጋና

የአምላኬን ፡ ጥበቃ ፡ አይቼአለሁ
በክንፉ ፡ ማረፍን ፡ ተምሬአለሁ
እንደ ፡ ዐይኑ ፡ ብሌን ፡ ጌታ ፡ ይጠብቀኛል
ክብር ፡ ለዘለዓለም ፡ ይገባዋል

አዝ፦ ምሥጋና ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ምሥጋና
ያደረከው ፡ ተዐምራትህን ፡ በዝቷልና
በመሰንቆ ፡ በከበሮ ፡ በበገና
ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ምሥጋና