እረኛዬ (Eregnaye)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሳዝን ፡ ስንገላታ ፡ ጠላትም ፡ ሲያጠቃኝ
ፈተና ፡ ሲከበኝ ፡ ቀን ፡ ሲጨልምብኝ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ልትረዳኝ ፡ የምትችል
ተስፋዬ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ሌላማ ፡ የለኝም

እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ መከታዬ
እንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ
ኢየሱሰ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ ፡ መከታዬ
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ

 ። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
 ። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
ደግፈኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ተራመድ
አላፊውን ፡ ደስታ ፡ ልቦናዬ ፡ እንዳይወድ

እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ መከታዬ
እንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ
ኢየሱሰ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ ፡ መከታዬ
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ

ስማኝ ፡ አፍቃሪዬ ፡ ስሞታዬን ፡ እንካ
ልቤ ፡ እንዳዘነብኝ ፡ ልብህም ፡ ይነካ
ሌላማ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ ቋሚ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ሃዘኔ ፡ ሚሰማው ፡ ልቡ ፡ የሚራራ

እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ መከታዬ
እንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ
ኢየሱሰ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ ፡ መከታዬ
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ

ሥጋ ፡ ደካማ ፡ ነው ፡ ሁሉንም ፡ ይመኛል
ስሜትም ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ ከውድቀት ፡ ያደርሳል
ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ ውድቀት ፡ ጠብቀኝ ፡ ጌታዬ
እምነቴ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ጥብቅ ፡ ነው ፡ መሪዬ

እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ እረኛዬ ፡ መከታዬ
እንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ
ኢየሱሰ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ ፡ መከታዬ
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አለኝታ ፡ ጠባቂዬ