እረኛችን ፡ ይጠብቀናል (Eregnachen Yitebeqenal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እረኛችን ፡ ይጠብቀናል
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ አስጥሎናል
ወጥመድ ፡ ተሰብሮ ፡ እኛ ፡ አምልጠናል
ረድኤታችን ፡ ተዋግቶልናል (፫x)

 
1. የጠላትን ፡ ፍላጻ ፡ ሰብሮ
እኛን ፡ የከለለ ፡ ፈጥኖ
ከቅጥራችን ፡ ኋላ ፡ የቆመው
የእሳት ፡ ነበልባል ፡ የሆነልን
ዘንዶውን ፡ ደርሶ ፡ ቀጠቀጠው
ወጥመዱን ፡ ሰብሮ ፡ ከእግራችን ፡ በታች ፡ ጣለው

አዝ፦ እረኛችን ፡ ይጠብቀናል
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ አስጥሎናል
ወጥመድ ፡ ተሰብሮ ፡ እኛ ፡ አምልጠናል
ረድኤታችን ፡ ተዋግቶልናል (፫x)

2. ሰልፉ ፡ ደርቶ ፡ ውጊያው ፡ ጠንክሮ
የጦሩ ፡ ሜዳ ፡ ደም ፡ ተነክሮ
ጠላት ፡ ሲያይል ፡ ጌታን ፡ ጠራነው
በውጊያው ፡ ሜዳ ፡ ቅደም ፡ አልነው
እርሱም ፡ በበቀል ፡ ከፍ ፡ አለልን
በአምላካችን ፡ ኃይል ፡ ከቅጥሩ ፡ በላይ ፡ ቆምን

 
አዝ፦ እረኛችን ፡ ይጠብቀናል
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ አስጥሎናል
ወጥመድ ፡ ተሰብሮ ፡ እኛ ፡ አምልጠናል
ረድኤታችን ፡ ተዋግቶልናል (፫x)

3. ሃሌሉያ ፡ ጌታ ፡ አድኖናል
ኢየሱስ ፡ በደሙ ፡ ሸፍኖናል
ከእርሱ ፡ ሽተን ፡ ትርፍ ፡ አላጣንም
በጠላት ፡ ወጥመድ ፡ አልገባንም
ዘንዶውን ፡ ደርሶ ፡ ቀጠቀጠው
ወጥመዱን ፡ ሰብሮ ፡ ከእግራችን ፡ በታች ፡ ጣለው

 
አዝ፦ እረኛችን ፡ ይጠብቀናል
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ አስጥሎናል
ወጥመድ ፡ ተሰብሮ ፡ እኛ ፡ አምልጠናል
ረድኤታችን ፡ ተዋግቶልናል (፫x)