እንፀናለን ፡ በጊዜውም ፡ ያለጊዜውም (Entsenalen Begiziewem Yalegiziewem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እንፀናለን ፡ በጊዜውም ፡ ያለጊዜውም
ዛሬ ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንፀናለን

ወደ ፡ እሣት ፡ ልንቃጠል
ዓይናችን ፡ እያየ ፡ ሲንበለበል
ዕውነትስ ፡ ጌታችን ፡ ወዲያ ፡ ካለልን
ለጅራፍ ፡ ጀርባችንን ፡ እንሰጣለን

አዝ፦ እንፀናለን ፡ በጊዜውም ፡ ያለጊዜውም
ዛሬ ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንፀናለን

አባቶችን ፡ በዕምነት ፡ ያቆመውን
በመጋዝ ፡ መሠንጠቅ ፡ ያጸናውን
ያ ፡ አምላካቸው ፡ ነው ፡ አምላካችን
የሚያፀና ፡ ጉልበት ፡ ታዳጊያችን

አዝ፦ እንፀናለን ፡ በጊዜውም ፡ ያለጊዜውም
ዛሬ ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንፀናለን

የከንቱ ፡ ቃላቶችን ፡ ደርዳሪ
አንሆንም ፡ በሥጋችን ፡ ፎካሪ
መንፈስ ፡ ያስቻለንን ፡ ልንቀበል
ተሸክመን ፡ አለን ፡ የእምነት ፡ መስቀል

አዝ፦ እንፀናለን ፡ በጊዜውም ፡ ያለጊዜውም
ዛሬ ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንፀናለን

ሲድራቅና ፡ ሚሳቅ ፡ አብደናጐን
ከቶን ፡ እረመጥ ፡ ውስጥ ፡ ያወጣውን
የሕዝቡን ፡ ጠላቶች ፡ የሚበቀል
ዛሬም ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ኃይል

አዝ፦ እንፀናለን ፡ በጊዜውም ፡ ያለጊዜውም
ዛሬ ፡ የጠበቀን ፡ ነገም ፡ አይተወንም
እንፀናለን