እኔስ ፡ ተስፋዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (Enies Tesfayie Eyesus New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የማየው ፡ ሁሉ ፡ አላፊ ፡ ነው
አልመኘውም ፡ ሆዴም ፡ አይባባ
ረጋፊ ፡ ነው ፡ ጠፊ ፡ አንደ ፡ አበባ

የምመካበት ፡ ያለም ፡ ዕውቀቴ
ያለኝም ፡ ሁሉ ፡ በምድር ፡ ንብረቴ
ጸንቶ ፡ የሚቆም ፡ በፍፁም ፡ የለም
በቅጽበት ፡ ኃይልም ፡ የሚጠፋ ፡ ነው

አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የማየው ፡ ሁሉ ፡ አላፊ ፡ ነው
አልመኘውም ፡ ሆዴም ፡ አይባባ
ረጋፊ ፡ ነው ፡ ጠፊ ፡ አንደ ፡ አበባ

በምድር ፡ መመኪያ ፡ የማደርጋቸው
አንድ ፡ ቀን ፡ ያልፋሉ ፡ አየኋቸው
የማያልፈውን ፡ ጸንቶ ፡ ኗሪውን
ላምልከው ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬን

አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የማየው ፡ ሁሉ ፡ አላፊ ፡ ነው
አልመኘውም ፡ ሆዴም ፡ አይባባ
ረጋፊ ፡ ነው ፡ ጠፊ ፡ አንደ ፡ አበባ

ደምቆ ፡ እየታየ ፡ ዛሬ ፡ ለጊዜው
ጸንቶ ፡ የሚኖር ፡ የሚመስለው
ነገ ፡ በቅጽበት ፡ የሚጠፋውን
አልታመንም ፡ እረጋፊውን

አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የማየው ፡ ሁሉ ፡ አላፊ ፡ ነው
አልመኘውም ፡ ሆዴም ፡ አይባባ
ረጋፊ ፡ ነው ፡ ጠፊ ፡ አንደ ፡ አበባ

ዘመን ፡ ቢለወጥ ፡ ያማይለወጥ
ጊዜ ፡ ሁኔታ ፡ ያማይቀሩት
እኔ ፡ ያማመልከው ፡ ኃይሉ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የማይረታ

አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የማየው ፡ ሁሉ ፡ አላፊ ፡ ነው
አልመኘውም ፡ ሆዴም ፡ አይባባ
ረጋፊ ፡ ነው ፡ ጠፊ ፡ አንደ ፡ አበባ