እኔ ፡ ኢየሱስን ፡ ለማየት (Enie Eyesusen Lemayet)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እኔ ፡ ኢየሱስን ፡ ለማየት ፡ ከቶ ፡ አይሆንልኝም
የእኔ ፡ ጠባይ ፡ ደካማ ፡ ነው ፡ የሚመራኝ ፡ ለጥፋት
ብርሃንን ፡ ለሁሉ ፡ ፍጥረት ፡ አብራልነ ፡ ለሕይወት
በዚህ ፡ ብቻ ፡ እመራለሁ ፡ በብፅዕናህ ፡ ለመግባት

እንዴት ፡ ያለ ፡ ሕይወት ፡ ሆነ ፡ ለተያዙ ፡ በመርገም
ከመከራ ፡ ቀንበር ፡ ሁሉ ፡ በሞተበት ፡ ቀን ፡ ወጡ
ስለዚህ ፡ ይጠራል ፡ አሁን ፡ በደሙ ፡ የተገዙትን
እየው ፡ እየው ፡ ጊዜ ፡ ሳለ ፡ ጨለማ ፡ ሳይደርስብህ

ማነው ፡ አሁን ፡ የሚጠራ ፡ እየጮኸ ፡ በፍቅር
ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ ሁላችሁ ፡ ፀጋዬን ፡ ተቀበሉ
እርሱ ፡ ነው ፡ መድኃኒታችን ፡ ስለ ፡ ዓለም ፡ የሞተ
ስለዚህ ፡ መጥራቱን ፡ አክብር ፡ ለዘለዓለም ፡ ልትድን