እንግዳ ፡ አለ ፡ በደጅ (Engeda Ale Bedej)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እንግዳ ፡ አለ ፡ በደጅ ፡ አስገባው
ከዚያ ፡ ብዙ ፡ ቆይቷል ፡ አስገባው
አስገባው ፡ ሳይሄድብህ ፡ አስገባው
ቅዱስ ፡ ጌታን ፡ ኢየሱስን
የአብን ፡ ልጅ ፡ አስገባው

ልብህን ፡ አሁን ፡ ክፈት ፡ አስገባው
ብትዘገይ ፡ ይሄዳል ፡ አስገባው
አስገባው ፡ ወዳጅህን ፡ ነፍስህን ፡ ይጠብቃል
እርሱ ፡ ይጠብቅሃል ፡ አስገባው

አሁን ፡ ምክሩን ፡ ተቀበል ፡ አስገባው
አሁን ፡ እርሱን ፡ ምረጠው ፡ አስገባው
አርሱ ፡ በደጅህ ፡ ቆሟል ፡ ደስታን ፡ ያመጣልሃል
ስሙንም ፡ ታከብራለህ ፡ አስገባው

ድግሥ ፡ ያደርግልሃል ፡ አስገባው
ይቅርታም ፡ ይሰጥሃል ፡ በዓለሙ ፡ ፍጻሜ
በሰማይ ፡ ያገባሃል ፡ አስገባው