እንስገድ ፡ ለአምላክ (Enesged Lamlak)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

poem>

እንስገድ ፡ ለአምላክ ፡ ለክብር ፡ ጌታ
እንዘምርም ፡ ፍቅሩን ፡ በደስታ
መጠጊያ ፡ ጋሻችን ፡ ፈጣሪያችን
ግርማን ፡ ተላብሷል ፡ እንዲሁም ፡ ምስጋናን


ኃይሉን ፡ አስታውቁ ፡ ደግሞም ፡ ጸጋውን
ዙፋኑ ፡ ጠፈር ፡ ልብሶቹም ፡ ብርሃን
ቁጣውን ፡ በነገድጓድ ፡ ድምጽ ፡ ያሰማል
በበረታ ፡ ሞገድ ፡ ኃይሉን ፡ ያሳያል


ተነግሮ ፡ አያልቅ ፡ የአንተ ፡ እርዳታ
ሊገኝ ፡ ይችላል ፡ በሁሉ ፡ ቦታ
ከሰማይ ፡ በረከትን ፡ ለምታፈስ
ለቸር ፡ አምላካችን ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ


እኛን ፡ ደካሞችን ፡ የአፈር ፡ ልጆችን
ያለአንተ ፡ ብርታት ፡ ተስፋ ፡ ዓይኖረንም
የአንተ ፡ ርህራሄ ፡ ጸንቶ ፡ ይኖራል
ለሰዎችም ፡ ሁሉ ፡ ተስፋ ፡ ይሰጣል

/poem>