እንሰብሰብ ፡ በሕይወት ፡ ውኃ (Enesebseb Behiwot Weha)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እንሰብሰብ ፡ በሕይወት ፡ ምንጭ
በጥሩ ፡ ውኃ ፡ ምንጭ
ኢየሱስ ፡ ይቀበለናል
ከዚያ ፡ መልካም ፡ አቀባበል

ኑ ፡ እንሰብሰብ
በሕይወት ፡ ምንጭ ፡ እንሰብሰብ (፪x)
በሕይወት ፡ ምንጭ
በዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ምንጭ

በጉዟችንም ፡ ስንደክም
ማረፍ ፡ ደስ ፡ ያሰኛል
ጥሩ ፡ ውኃ ፡ በሚፈልቅበት
ከሚፈለፍል ፡ ምንጭ

ኑ ፡ እንሰብሰብ
በሕይወት ፡ ምንጭ ፡ እንሰብሰብ (፪x)
በሕይወት ፡ ምንጭ
በዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ምንጭ

ወደ ፡ ኢየሱስም ፡ ብንመጣ
ኃይላችንን ፡ ያድሳል
የማዳኑን ፡ ደስታ ፡ እንቅመስ
ከሚፈለፍል ፡ ምንጭ

ኑ ፡ እንሰብሰብ
በሕይወት ፡ ምንጭ ፡ እንሰብሰብ (፪x)
በሕይወት ፡ ምንጭ
በዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ምንጭ