እንገዛልሃለን (Engezalehalen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እንገዛልሃለን ፡ እንሰግድልሃለን
ሞገስህ ፡ ብዙ ፡ ነው
በዐይናችን ፡ ያየነው

ታላቅ ፡ ተራራ ፡ ጐልቶ ፡ የታየው
ኃይሉ ፡ አክትሞ ፡ ፈርሶ ፡ አየነው
አንተ ፡ ግን ፡ ሁሉን ፡ አሸንፈሃል
እናመልክህ ፡ ዘንድ ፡ ይህን ፡ አርገሃል

አዝ፦ እንገዛልሃለን ፡ እንሰግድልሃለን
ሞገስህ ፡ ብዙ ፡ ነው
በዐይናችን ፡ ያየነው

ተግሳጽን ፡ የተቀበለው ፡ ህዝብህ
እራሱን ፡ አዋርዶ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ሲያይህ
አበሳውን ፡ በእርግጥ ፡ ተመልክተሃል
ሁሉ ፡ የተቻለህ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል

አዝ፦ እንገዛልሃለን ፡ እንሰግድልሃለን
ሞገስህ ፡ ብዙ ፡ ነው
በዐይናችን ፡ ያየነው

የኃያላን ፡ ትዕቢት ፡ ክብር ፡ ዕውቀቱ
በድንገት ፡ ሲሻር ፡ ሲቀር ፡ አጥንቱ
የጽዮን ፡ ውብ ፡ ሆይ ፡ ነፍሴ ፡ ታክብር
ስግደት ፡ ሚገባህ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ

አዝ፦ እንገዛልሃለን ፡ እንሰግድልሃለን
ሞገስህ ፡ ብዙ ፡ ነው
በዐይናችን ፡ ያየነው

የእንባ ፡ ሚዛን ፡ ዋጋ ፡ ተምነህ
የጠላት ፡ ጭፍራን ፡ ስሩን ፡ ነቃቅለህ
ቀና ፡ አድርገህ ፡ አስኪደኸናል
ኤልሻዳይ ፡ ንጉሥ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል

አዝ፦ እንገዛልሃለን ፡ እንሰግድልሃለን
ሞገስህ ፡ ብዙ ፡ ነው
በዐይናችን ፡ ያየነው