እንዴት ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ (Endiet Yale Wedaj Alegn)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
እንዴት ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ?
አስቀድሞ ፡ ወደደኝ
በፍቅሩ ፡ ወደርሱ ፡ ሳበኝ
ወደርሱ ፡ አቀረበኝ
በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ አሰረኝ
ሊፈታ ፡ በማይቻል
እኔ ፡ የእርሱ ፤ እርሱም ፡ የእኔ
እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ድረስ
እንዴት ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ?
ደሙን ፡ አፈሰሰልኝ
ሕይወቱን ፡ ብቻ ፡ አይደለም
ራሱንም ፡ ደግሞ ፡ ሰጠኝ
የራሴ ፡ አንዳች ፡ የለኝም
የፈጣሪዬ ፡ እንጂ
ልቤ ፡ ብርታቴ ፡ ሕይወቴ
የእርሱ ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም
እንዴት ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ?
ኃይል ፡ ሁሉ ፡ የተሰጠው
በሕይወት ፡ መንገድ ፡ ሊመራኝ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ሊያደርሰኝ
የዘለዓለም ፡ ክብር ፡ ታየኝ
እኔን ፡ ሊያደፋፍረኝ
አሁንም ፡ በትጋት ፡ ልሥራ
ለዘለዓለም ፡ እንዳርፍ
እንዴት ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ?
ቸር ፡ ዕውነተኛ ፡ ታጋሽ
ጠቢብ ፡ መካር ፡ ፈቃር ፡ መሪ
ለሚወዱት ፡ ጋሻ ፡ ነው
ከብርቱ ፡ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ
ማን ፡ ሊለየኝ ፡ ይችላል?
በሞት ፡ ሆነ ፡ በሕይወትም
ለዘለዓለም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ
|