እንዴት ፡ የሚገርም ፡ ነው (Endet Yemigerm Niew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እንዴት ፡ የሚገርም ፡ ነው? ኦ! ቸር ፡ መድኅኔ
በደምህ ፡ መድኃኒት ፡ ተገኘ ፡ ለእኔ
ከፍርድ ፣ ከቅጣትም ፡ ነፃነት ፡ ላገኝ
የመድኃኒቴ ፡ ቁስል ፡ ከሞት ፡ ፈወሰኝ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ፍቅሩ
ዕሙንም ፡ ምክሩ
ፀጋውንም ፡ ዘምሩ
ይስፋ ፡ ክብሩ

እንዴት ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ተሰጥቶኛል
እርሱም ፡ በቸርነት ፡ ተቀብሎኛል
ዓርነት ፡ አወጣኝ ፡ ለሰይጣን ፡ ሥልጣን
ድኜም ፡ ልመላለስ ፡ በፊቱ ፡ ብርሃን
ታላቅ ፡ ነው ፡ ፍቅሩ
ዕሙንም ፡ ምክሩ
ፀጋውንም ፡ ዘምሩ
ይስፋ ፡ ክብሩ

ኦ! መድኅኔ ፡ ደምህ ፡ እንዴት ፡ ክቡር ፡ ነው?
ለቁስሌ ፡ ሁሉ ፡ መድኃኒቱ ፡ ነው
ሥቃዬንም ፡ ሁሉ ፡ ይፈውሰዋል
ዕንባዬንም ፡ መድኃኒቴ ፡ ያብሰዋል
ታላቅ ፡ ነው ፡ ፍቅሩ
ዕሙንም ፡ ምክሩ
ፀጋውንም ፡ ዘምሩ
ይስፋ ፡ ክብሩ

ለእኔ ፡ የተሰቀልኸው ፡ ላመስግንህ
ኦ! ጌታዬ ፡ አምላኬም ፡ ንጉሤ ፡ ነህ
ሥጋዬም ፡ ሲቀበር ፡ በተስፋ ፡ ልረፍ
የማዳንህን ፡ ኃይል ፡ ለመመልከት ፡ ልትረፍ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ፍቅሩ
ዕሙንም ፡ ምክሩ
ፀጋውንም ፡ ዘምሩ
ይስፋ ፡ ክብሩ