እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥም ፡ አይገኝም (Ende Eyesus Sem Aygegnem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥም ፡ አይገኝም
ይህ ፡ የተወደደ ፡ ስም
ለመላእክትም ፡ ደስታ ፡ ነው
ለክርስቲያንም ፡ ተድላ ፡ ነው

አዝማች
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም

እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥም ፡ አይገኝም
የሰው ፡ ልብ ፡ ሲያዝን ፡ ሳለ
ሌላ ፡ እንደርሱ ፡ ሥም ፡ የለም
ደስታ ፡ ለልብ ፡ የሚሰጥ

አዝማች
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም

እንደማየው ፡ ተስፋ ፡ አለኝ
በደመና ፡ ሲገለጥ
ድምጹን ፡ መስማት ፡ ተስፋዬ ፡ ነው
ከጥማቴ ፡ ሊያረካኝ

አዝማች
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም

እንድሠራለት ፡ ቢፈልግ
ቀን ፡ በቀን ፡ በዓለም ፡ ውስጥ
ዕርዳታውንም ፡ ከሰጠኝ
ጠንክሬ ፡ እሠራለሁ

አዝማች<
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም