እንዳንተ ፡ ማነው? (Endante Manew?)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ክብር ፡ ይሻራል ፡ ውበት ፡ ይጠፋል
ሃብትም ፡ ይበናል
አበባው ፡ ረግፎ ፡ ሲጠወላልግ
ትላንት ፡ ያየነው ፡ ለዛሬ ፡ ሲደርቅ
አንተ ፡ ብቻ ፡ አትለዋወጥ
እጅግ ፡ ዕጹብ ፡ ድንቅ

አዝ፦ በኃይል ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኃይል
በክብር ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ክቡር
በስልጣን ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃያል (፪x)

በምድር ፡ ክበቦች ፡ ላይ ፡ የሚራመድ
ሰማይ ፡ ተቀምጦ ፡ ምድር ፡ የሚረግጥ
ከድ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ጌታ
እንዳንተ ፡ ማነው ፡ በቀን ፡ በማታ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ የሁሉ ፡ ጌታ

አዝ፦ በኃይል ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኃይል
በክብር ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ክቡር
በስልጣን ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃያል (፪x)

የእስራኤል ፡ ታቦት ፡ ጠላቶች ፡ ማርከውት
አማሌቅ ፡ መሃል ፡ ይቀመጥ ፡ ብለው
አማልክት ፡ ሁሉ ፡ ሲሰባበሩ
ዳጐን ፡ ሲወድቅ ፡ ሲናቅ ፡ ባገሩ
የእስራኤል ፡ ታቦት ፡ በአሸናፊነት ፡ ገባ ፡ በክብሩ

አዝ፦ በኃይል ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኃይል
በክብር ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ክቡር
በስልጣን ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃያል (፪x)