እናምናለን ፡ በመስቀሉ (Enamnalen Bemesqelu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እናምናለን ፡ በመስቀሉ
እንቆማለን ፡ በወንጌሉ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ይሠራል
አልተለወጠም ፡ ቃሉ

የኃጢአት ፡ ይቅርታ ፡ የሚሰጠው ፡ ደሙ
ፈውሥም ፡ የሚያመነጨው ፡ የመስቀል ፡ ሕመሙ
ሙሉ ፡ ወንጌላችንን ፡ እንመካበታለን
ጠላትን ፡ ለመቋቋም ፡ ከቃሉ ፡ ኃይል ፡ አለን

አዝ፦ እናምናለን ፡ በመስቀሉ
እንቆማለን ፡ በወንጌሉ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ይሠራል
አልተለወጠም ፡ ቃሉ

የፍቅሩን ፡ የምሥራች ፡ ከወንጌሉ ፡ ሰምተናል
ኢየሱስ ፡ አዳኝ ፡ መሆኑን ፡ አምነን ፡ ተቀብለናል
ያልታወቀውን ፡ ምሥጢር ፡ ተረዳን ፡ ከቃሉ
እርሱ ፡ ንጉሥ ፡ መሆኑን ፡ በፍጥረት ፡ ላይ ፡ ሁሉ

አዝ፦ እናምናለን ፡ በመስቀሉ
እንቆማለን ፡ በወንጌሉ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ይሠራል
አልተለወጠም ፡ ቃሉ

ያመነ ፡ የተጠመቀ ፡ በሥሙ ፡ ይድናል
ያላመነ ፡ ደግሞ ፡ ይፈረድበታል
እንድንቀበለው ፡ ነው ፡ ደሙ ፡ ከኢየሱስ ፡ መፍሰሱ
ሕይወትን ፡ ከቶ ፡ ማግኘት ፡ አይቻልም ፡ ያለእርሱ

አዝ፦ እናምናለን ፡ በመስቀሉ
እንቆማለን ፡ በወንጌሉ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ይሠራል
አልተለወጠም ፡ ቃሉ

የጥበብ ፡ መጀመሪያ ፡ የነገር ፡ ሁሉ ፡ ማኅደር
ደኅንነትን ፡ የሚያውጅ ፡ ሰላምን ፡ የሚናገር
የነጠረ ፡ ቃል ፡ ያለው ፡ በእሣት ፡ የተፈተነ
ክቡር ፡ ነው ፡ ወንጌላችን ፡ በዓለማችን ፡ የገነነ

አዝ፦ እናምናለን ፡ በመስቀሉ
እንቆማለን ፡ በወንጌሉ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ይሠራል
አልተለወጠም ፡ ቃሉ