እናምናለን ፡ በአባት (Enamnalen BeAbat)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እናምናለን ፡ በአባት
ያቆመ ፡ ምድርን ፡ ሰማያት
ጥጋችን ፡ ነው
ርሕሩህ ፡ የዋሕ ፡ለሰው
ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ ጸባዖት

ሊያድነን ፡ ከሞት ፡ ጥፋት
ክርስቶስ ፡ መጣልን ፡ ከአባት
እኛን ፡ ፈታ
ሆነልን ፡ ቸር ፡ ጌታ
ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ ጸባዖት

መንፈሱ ፡ ፀጋን ፡ ያድላል
ይቀድሰናል ፡ በአምላክ ፡ ቃል
ለነፍስ ፡ ሕይወት
ይሰጣል ፡ በዕምነት
ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ ጸባዖት