እናመሰግንሃለን (Enamesegenehalen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከጨለማ ፡ ወጥተን ፡ ብርሃን ፡ በርቶልናል
ከሞት ፡ ጥላ ፡ ሃገር ፡ ፍቅርህ ፡ መልሶናል
ከወይኑ ፡ ግንድ ፡ ገብተን ፡ ጣዕም ፡ አግኝተናል
ለመልካምም ፡ ፍሬ ፡ ተክለኸናል

አዝ፦ እናመሰግንሃለን
እናመሰግንሃለን
እናመሰግንሃለን ፡ ጌታ

ማንም ፡ ሳይጐበኘን ፡ ሳያስበን ፡ ገና
ህመምተኞች ፡ ሆነን ፡ ደዌያችን ፡ የጠና
በማጽናናት ፡ ቃል ፡ በቁስልህ ፡ ፈወስከን
ከመውደቅ ፡ ከመፍረስ ፡ ከጥፋት ፡ አዳንከን

አዝ፦ እናመሰግንሃለን
እናመሰግንሃለን
እናመሰግንሃለን ፡ ጌታ

ለደንቆሮ ፡ መስማት ፡ ለዕውራን ፡ ማየትን
ለሞቱት ፡ መነሳት ፡ ኃይልና ፡ ብርታትን
ስትሰጥ ፡ ክንድህን ፡ አይተን ፡ ተማርከናል
የእጆችህን ፡ ስራ ፡ ጉልበቱን ፡ አውቀናል

አዝ፦ እናመሰግንሃለን
እናመሰግንሃለን
እናመሰግንሃለን ፡ ጌታ