From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ
ለደካማው ፡ ሃይልህን ፡ ልትሰጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
መራራውን ፡ ሕይወት ፡ ልታጣፍጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
የደነደነውን ፡ ልብ ፡ ልትለውጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ
የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ትከፍታለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
የነሃሱንም ፡ መዝጊያ ፡ ትሰብራለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በጭንቀት ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ ትሆናለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ
ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ታደርጋለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ሸለቆውን ፡ ውኃ ትሞላለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ትሆናለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ
ከፋንድያ ፡ ከአመድ ፡ ታነሳለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በግ ፡ ጠባቂን ፡ ንጉሥ ፡ ታደርጋለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
በመቶ ፡ አመት ፡ ልጅን ፡ ትሰጣለህ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ
ሰማይንም ፡ ልትለካ ፡ በስንዝር ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ውሆችንም ፡ በእፍኝህ ፡ ልትሰፍር ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ
መራራውን ፡ ሕይወት ፡ ልታጣፍጥ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
የተዘጋን ፡ ማህጸን ፡ ልትከፍት ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
መካኒቷን ፡ በልጅ ፡ ልትባርክ ፤ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ
አዝ፦ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይነህ (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ
|