እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን (Ejun Zergeto Gieta Bayredan)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ
በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ
ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ሆኖ ፡ አስጥሞን
ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን

የሞትን ፡ ፍርድ ፡ ብዙ ፡ ሰምቶናል
በሕይወቴ ፡ ለመኖር ፡ ዕለት ፡ ሞተናል
የኢየሱስን ፡ ሞት ፡ ተሸግመን ፡ ዞረናል
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ በምህረቱ ፡ ኖረናል

አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ
በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ
ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ሆኖ ፡ አስጥሞን
ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን

በእምነት ፡ እንጂ ፡ በምናየው ፡ አይደለም
ከጌታ ፡ በቀን ፡ እኛ ፡ ትምክህት ፡ የለንም
ጽድቃችን ፡ እንኳን ፡ ለዚህ ፡ አላበቃንም
ፀጋው ፡ እጽንቶን ፡ ከእርሱ ፡ አልተለየንም

አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ
በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ
ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ሆኖ ፡ አስጥሞን
ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን

ሕያዋን ፡ ሆነን ፡ በእርሱ ፡ እንኖራለን
የጌታን ፡ ስራ ፡ ዛሬም ፡ አንገልጻለን
ክብር ፡ ለስሙ ፡ ሞገስ ፡ ለስሙ ፡ ብለን
ያለንን ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እንሰዋለን