እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ (Ejeg Yemimer Yemirara)
From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ
አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)
ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፪x)
በአንድ ፡ ላይ ፡ ተስማምተው ፡ እውነትና ፡ ምህረት (፪x)
መግባት ፡ ተቻለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ባለበት (፪x)
ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ ሲሆን ፡ እንከን ፡ የሌለበት (፪x)
አልፈረደብኝም ፡ ምሕረቱ ፡ አይሎበት (፪x)
እንኳንስ ፡ ምረኸኝ ፡ ቀርቶልኝ ፡ አበሳ (፪x)
እኔስ ፡ ምሥጋናህን ፡ ምንጊዜም ፡ አልረሳ (፪x)
በምህረቱ ፡ ጋሻ ፡ እየከለልን (፪x)
ካዳነን፡ በኋላ ፡ ምሕረቱ ፡ ያዘን (፪x)
|