እጅ ፡ ለእጃችን (Ej Lejachen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እጅ ፡ ለእጃችን ፡ ተያይዘን
ኢየሩሳሌም ፡ እንገባለን
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ አንድ ፡ ሆነናል
አንለያይም ፡ ተዋደናል

መልክና ፡ ጐሳ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ ዕውቀት
ከቶ ፡ አይለየንም ፡ ከያዝነው ፡ እምነት
በቀራኒዮ ፡ በፈሰሰው ፡ ደም
ከእንግዲህ ፡ አንድ ፡ ነን ፡ ሰይጣንም ፡ ይፈር

አዝ፦ እጅ ፡ ለእጃችን ፡ ተያይዘን
ኢየሩሳሌም ፡ እንገባለን
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ አንድ ፡ ሆነናል
አንለያይም ፡ ተዋደናል

በመሃላችን ፡ ገደብ ፡ ዐይኖርም
አጥር ፡ ግድግዳ ፡ አይሰራም ፡ ማንም
የኢየሱስ ፡ ደም ፡ አንድ ፡ አድርጐናል
እንዘምራለን ፡ ሃሌ ፡ ሉያ ፡ አያልን

አዝ፦ እጅ ፡ ለእጃችን ፡ ተያይዘን
ኢየሩሳሌም ፡ እንገባለን
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ አንድ ፡ ሆነናል
አንለያይም ፡ ተዋደናል

ታላቅም ፡ ታናሽ ፡ ክፉ ፡ ጨዋ ፡ የለም
ሁሌ ፡ አንድ ፡ ሆኗል ፡ በክርስቶስ ፡ መስቀል
አባትና ፡ ልጅ ፡ አንድ ፡ እንደሆኑ
እኛም ፡ አንድ ፡ ሆንን ፡ ሲወርድ ፡ መንፈሱ

አዝ፦ እጅ ፡ ለእጃችን ፡ ተያይዘን
ኢየሩሳሌም ፡ እንገባለን
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ አንድ ፡ ሆነናል
አንለያይም ፡ ተዋደናል

እንደመልካችን ፡ የሁሉ ፡ ጠባይ
ሁሌ ፡ አንድ ፡ ባይሆን ፡ ምንም ፡ ቢለያይ
ግን ፡ በውስጣችን ፡ የያዝነው ፡ ጌታ
እርሱ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ አንድነን ፡ በቃ

አዝ፦ እጅ ፡ ለእጃችን ፡ ተያይዘን
ኢየሩሳሌም ፡ እንገባለን
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ አንድ ፡ ሆነናል
አንለያይም ፡ ተዋደናል

የእግዚአብሔርን ፡ ስራ ፡ እንሰራለን
እርስ ፡ በእርሳችን ፡ አንድ ፡ ልብ ፡ ሆነን
በፍፁም ፡ የለም ፡ የሚያግደን
የመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ችቦን ፡ አንድደን

አዝ፦ እጅ ፡ ለእጃችን ፡ ተያይዘን
ኢየሩሳሌም ፡ እንገባለን
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ አንድ ፡ ሆነናል
አንለያይም ፡ ተዋደናል