From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ገና ፡ እግዚአብሔር ፡ ይሠራል ፡ ገና ፡ ምኑን ፡ አየንና
እንግዳ ፡ ሥራውን ፡ ከቶ ፡ ያልታወቀውን
በሰዎች ፡ አዕምሮ ፡ ያልተገመተውን
እናያለን ፡ ገና ፡ ድንቅ ፡ ሥራውን ፡ ሲሰራ
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
የተበተነውን ፡ ሕዝብ ፡ ይሰበስበዋል
በበረከት ፡ እጁ ፡ ከክፉ ፡ ያድነዋል
የተጠማች ፡ ነፍሱን ፡ እጅግ ፡ ያረካዋል
ለቅሶውን ፡ በደስታ ፡ ለውጦ ፡ ያጽናናዋል
አዝ፦ ገና ፡ እግዚአብሔር ፡ ይሠራል ፡ ገና ፡ ምኑን ፡ አየንና
እንግዳ ፡ ሥራውን ፡ ከቶ ፡ ያልታወቀውን
በሰዎች ፡ አዕምሮ ፡ ያልተገመተውን
እናያለን ፡ ገና ፡ ድንቅ ፡ ሥራውን ፡ ሲሰራ
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
የበጐነት ፡ ዐይኑን ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ያደርጋል
በሰጠንም ፡ ምድር ፡ በጽኑ ፡ ይተክለናል
እርሱንም ፡ የሚያውቅ ፡ ልብ ፡ ለእኛ ፡ ይሰጠናል
የከበረ ፡ ስሙን ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ያጠራል
አዝ፦ ገና ፡ እግዚአብሔር ፡ ይሠራል ፡ ገና ፡ ምኑን ፡ አየንና
እንግዳ ፡ ሥራውን ፡ ከቶ ፡ ያልታወቀውን
በሰዎች ፡ አዕምሮ ፡ ያልተገመተውን
እናያለን ፡ ገና ፡ ድንቅ ፡ ሥራውን ፡ ሲሰራ
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
ዳርቻችንንም ፡ ጌታችን ፡ አስፍቶ
ቁጥራችንን ፡ ደግሞ ፡ አብዝቶ ፡ አበርክቶ
ምሽጉን ፡ አፍርሶ ፡ ጠላትን ፡ አሳዶ
አይቀር ፡ ያሳየናል ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አውርዶ
አዝ፦ ገና ፡ እግዚአብሔር ፡ ይሠራል ፡ ገና ፡ ምኑን ፡ አየንና
እንግዳ ፡ ሥራውን ፡ ከቶ ፡ ያልታወቀውን
በሰዎች ፡ አዕምሮ ፡ ያልተገመተውን
እናያለን ፡ ገና ፡ ድንቅ ፡ ሥራውን ፡ ሲሰራ
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
ከለመንነውና ፡ ከአሰብነው ፡ ይልቅ
እጅግ ፡ አስበልጦ ፡ ለሚቻለው ፡ ማድረግ
ለእርሱ ፡ ከዘለዓለም ፡ እስከዘለዓለም
ክብርና ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ ፡ እንላለን
አዝ፦ ገና ፡ እግዚአብሔር ፡ ይሠራል ፡ ገና ፡ ምኑን ፡ አየንና
እንግዳ ፡ ሥራውን ፡ ከቶ ፡ ያልታወቀውን
በሰዎች ፡ አዕምሮ ፡ ያልተገመተውን
እናያለን ፡ ገና ፡ ድንቅ ፡ ሥራውን ፡ ሲሰራ
ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
|