እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ (Egziabhier Yemesgen Elalehugn)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
በበረሃ ፡ ስጓዝ ፡ ሲደርስብኝ ፡ ጉዳት
ረሃብና ፡ ጥማት ፡ ሕይወቴን ፡ ሲይዛት
ማነው ፡ ያዘነልኝ ፡ ወድቄ ፡ እንዳልቀር?
የደገፈኝ ፡ ማነው ፡ እንዳልሰባበር?
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
በመከራ ፡ ሥቃይ ፡ ነፍሴ ፡ ስትጨነቅ
ልቤ ፡ በፍርሃት ፡ በሃዘን ፡ ሲጥለቀለቅ
በድካም ፡ ተይዤ ፡ ወጀብ ፡ ሲያንገላታኝ
በቃልህ ፡ ታምኜ ፡ እንድቆም ፡ አደረግኸኝ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
ጠልቀው ፡ በማያውቁት ፡ ውስጣዊ ፡ ሕይወቴን
ሲያወጉ ፡ እየሰማሁ ፡ የእኔን ፡ ከንቱነቴን
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ድልን ፡ ሰጠኸኝ
ደካማ ፡ ምስኪኑን ፡ ለክብርህ ፡ አቆምኸኝ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
|