እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (Egziabhier Yemesgen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከውድቀት ፡ አነሳኝ
ከውድቀት ፡ አነሳኝ ፡ ጌታ ፡ ጌታ
እጁን ፡ ዘረጋና ፡ ከአዘቅት ፡ አወጣኝ
ስለዚህ ፡ ወደድኩት ፡ ማረኝ
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ በጣም
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ በጣም
የሞት ፡ ዕዳ ፡ ስለነበረብኝ
ኢየሱስ ፡ ከፈለልኝ

እንግዲህ ፡ ወንድሞች ፡ ሰውነታችሁን
መስዋዕት ፡ አድርጋችሁ ፡ አምጡ ፡ አምጡ
ከጌታችን ፡ ፈቃድ ፡ ክልል ፡ እንዳትወጡ
ሙሉ ፡ ልባችሁን ፡ ስጡ
ከነፍስ ፡ የመነጨ ፡ ፍሬ
እቅርቡ ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬ
ሰባራውን ፡ መንፈስ ፡ ይጠግናል
ጌታ ፡ ይወደናል

እንግዲህ ፡ እህቶች ፡ ለጌታ ፡ ተገዙ
የዓለም ፡ ነገሮችን ፡ ተዉ ፡ ተዉ
ከጌታችን ፡ ጋራ ፡ በየአለቱ ፡ ኑሩ
ሙሉ ፡ ልባችሁን ፡ ስጡ
ከነፍስ ፡ የመነጨ ፡ ፍሬ
አቅርቡ ፡ ምሥጋና ፡ ዛሬ
ሰባራውን ፡ መንፈስ ፡ ይጠግናል
ጌታ ፡ ይወደናል