እግዚአብሔር ፡ ይባረክ (Egziabhier Yebarek)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. የጠላት ፡ ሠራዊት ፡ ዙሪያህን ፡ ሲከብህ
የኃጢአት ፡ ማዕበል ፡ ነፍስን ፡ ሲያሰጨንቅ
አምላክህን ፡ ጥራው ፡ እሱ ፡ ይሰማሃል
አስጨናቂዎችን ፡ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ ይጥላል ።

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይባረክ
የነ ፡ አብርሃም ፡ አምላክ

2. የእግዚአብሔር ፡ ዓይኖች ፡ ወደ ፡ ጻድቃን ፡ ናቸው
ጆሮዎቹም ፡ ደግሞ ፡ ወደ ፡ ጩኸታቸው
ወደ ፡ አምላክ ፡ እጅሀን ፡ ተማጸን ፡ ይልሃል
አንተ ፡ የማታውቀውን ፡ ኃይሉን ፡ ያሳይሃል ።

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይባረክ
የነ ፡ ዳንኤል ፡ አምላክ

3. አምላክ ፡ በዙሪያችን ፡ ቅጥር ፡ ከሆነልን
ማንንም ፡ አንፈራም ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
የዘመናት ፡ አምላክ ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ
ኃያላችን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ከቶ ፡ የማይረታ ።

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ይባረክ
ታላቁ ፡ የእኛ ፡ አምላክ