እግዚአብሔር ፡ ለእኔ (Egziabhier Lenie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው (፪x)
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፍስ ፡ ሐሩር ፡ ቢመጣ ፡ መቼ ፡ እፈራለሁ
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፋስ ፡ ሐሩር ፡ ቢበዛ ፡ መች ፡ እናወጣለሁ

የሚያስተማምነውን ፡ ክንዱን ፡ ተመርኩዤ (፪x)
እኔን ፡ የያዘኝን ፡ ያንን ፡ እጁን ፡ ይዤ (፪x)
መቼ ፡ እፈራለሁ ፡ በሞት ፡ ጥላ ፡ ባልፍ (፪x)
አምላክ ፡ አለኝና ፡ ልብን ፡ የሚያሳርፍ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው (፪x)
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፍስ ፡ ሐሩር ፡ ቢመጣ ፡ መቼ ፡ እፈራለሁ
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፋስ ፡ ሐሩር ፡ ቢበዛ ፡ መች ፡ እናወጣለሁ

በሚሆነው ፡ ነገር ፡ ከቶም ፡ አልደነገጥ (፪x)
ተደላድያለሁ ፡ ፍፁም ፡ ላልናወጥ (፪x)
አውቃለሁኝና ፡ የታመንኩበትን (፪x)
እደገፈዋለሁ ፡ በሕይወቴ ፡ ዘመን (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው (፪x)
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፍስ ፡ ሐሩር ፡ ቢመጣ ፡ መቼ ፡ እፈራለሁ
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፋስ ፡ ሐሩር ፡ ቢበዛ ፡ መች ፡ እናወጣለሁ

በሰማይ ፡ ተቀምጦ ፡ ምድርን ፡ የሚገዛው (፪x)
የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ ለእኔስ ፡ ድጋፌ ፡ ነው (፪x)
ነፍሴ ፡ በአምላኳ ፡ ታምና ፡ ተቀምጣለች (፪x)
ከመከራም ፡ ሥጋት ፡ ከጭንቀት ፡ አርፋለች (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው (፪x)
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፍስ ፡ ሐሩር ፡ ቢመጣ ፡ መቼ ፡ እፈራለሁ
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ስሬን ፡ ሰድጃለሁ
ነፋስ ፡ ሐሩር ፡ ቢበዛ ፡ መች ፡ እናወጣለሁ