እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ከሰው ፡ ትለያለህ (Egziabhier Hoy Kesew Teleyaleh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
ከሰው ፡ ትለያለህ
ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ታደርጋለህ
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ትሆናለህ

የልቤ ፡ ሃሣብ ፡ እጅግ ፡ የከበደ
ፊቴ ፡ ዙሪያ ፡ ተጋድሞ ፡ የነበረ
ለካ ፡ በርግጥ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነው
በተዓምራት ፡ መሻቴን ፡ ፈፀመው

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
ከሰው ፡ ትለያለህ
ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ታደርጋለህ
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ትሆናለህ

እሾሃማ ፡ ነበር ፡ ቆንጥራማ
ያለፍኩበት ፡ ክፉ ፡ መንገድማ
ጥሼዋለሁ ፡ ንቡም ፡ አልነደፈኝ
ውዴ ፡ አምላኬ ፡ በክንዱ ፡ ሸፈነኝ

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
ከሰው ፡ ትለያለህ
ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ታደርጋለህ
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ትሆናለህ

መጨነቄ ፡ ተስፋዬን ፡ መቁረጤ
አልረባኝም ፡ ማጉረምረም ፡ በውስጤ
ለእኔስ ፡ በርግጥ ፡ ከብዶኝ ፡ ነበር
በጌታ ፡ አየሁ ፡ ሰምሮ ፡ ሁሉ ፡ ነገር

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
ከሰው ፡ ትለያለህ
ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ታደርጋለህ
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ትሆናለህ

ማዕበሉ ፡ የሚታዘዝለት
ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት
እርሱን ፡ ታምኖ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ ተረቷል?
ከእግሩ ፡ በታች ፡ ሁሉን ፡ ረግጦ ፡ ገዝቷል

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
ከሰው ፡ ትለያለህ
ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ታደርጋለህ
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ትሆናለህ