እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነህ (Egziabhier Hoy Endiet Denq Neh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነህ
ነፍሳችን ፡ ረካች ፡ በጉብኝትህ
ጥያቄያችንም ፡ ተመለሰልን
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን

ጠላት ፡ ጠፍሮ ፡ ፍፁም ፡ ተብትቦ
እንዳናመልክህ ፡ ዙሪያው ፡ ተክቦ
መሰንቆአችንን ፡ ከሰቀልንበት
ዛሬ ፡ አውርደን ፡ ንገሥ ፡ አልንበት

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነህ
ነፍሳችን ፡ ረካች ፡ በጉብኝትህ
ጥያቄያችንም ፡ ተመለሰልን
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን

እኛስ ፡ ቆዝመን ፡ አዝነንም ፡ ነበር
ማየት ፡ ተስኖን ፡ ከሞት ፡ ባሻገር
በትንሳኤው ፡ ኃያል ፡ ደስታን ፡ ሞልተኸን
በባዕድ ፡ ምድር ፡ እንዘምራለን

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነህ
ነፍሳችን ፡ ረካች ፡ በጉብኝትህ
ጥያቄያችንም ፡ ተመለሰልን
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን

ከአቻምና ፡ አምና ፡ ከአምናም ፡ ዘንድሮ
የአንተ ፡ ቸርነት ፡ ስንቱ ፡ ተቆጥሮ
ስንቱን ፡ ጨለማ ፡ አሸጋገርከን
ከምንገምተው ፡ በላይ ፡ ሆንክልን

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነህ
ነፍሳችን ፡ ረካች ፡ በጉብኝትህ
ጥያቄያችንም ፡ ተመለሰልን
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ከፍ ፡ ይበልልን