እግዚአብሔር ፡ ኃያል (Egziabhier Hayal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

ሕዝቡን ፡ ከልሎ ፡ የሚዋጋ ፡ ለጠላት ፡ ዛቻ ፡ የማይሰጋ
ብድራቱን ፡ መላሽ ፡ የእኛ ፡ አምላክ
ይረታ ፡ እንጂ ፡ መረታትን ፡ አያውቅ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

የእምነት ፡ ባለድል ፡ ሳይጸጸት
ጌታውን ፡ አምኖ ፡ ሳያፍርበት
ለተስፋውም ፡ ለብሶ ፡ ሰንሰለት
ሕይወቱን ፡ ሰጥቷል ፡ ሳይሰስት (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

አንተም ፡ በኃይሉ ፡ ድል ፡ ነስተህ
በእቶን ፡ ተፈትነህ ፡ ነጥረህ
ለመንግሥቱ ፡ ብቁ ፡ ሆነህ
እንድትወጣ ፡ ጌታ ፡ ይርዳህ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል

ያን ፡ ጊዜ ፡ ተዋግቶ ፡ የረታ
የጠላቱን ፡ ጅማት ፡ የፈታ
በጽኑ ፡ አመታት ፡ የሚመታ
ሁሉን ፡ የሚችል ፡ የድል ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከዛሬ ፡ በማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል