እግዚአብሔር ፡ በሰማይ ፡ ተባረክ (Egziabhier Besemay Tebarek)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
እግዚአብሔር ፡ በሰማይ ፡ ተባረክ (፪x)
ተባረክ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ዘላለም
መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ
በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ
በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አቁሞኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል
ላከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን ፡
የታለ ፡ እልልታ ፡ ጭብጨባው
ለኢየሱስ ፡ የሚገባው
የከፈለው ፡ እዳችንን ፡ ያዳናት ፡ ነፍሳችንን
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ምስጋና ፡ እርሱ ፡ አምላካችን ፡ ነውና
ጨለማውን ፡ የገፈፈው ፡ ክብር ፡ ምስጋና ፡ ይድረሰው
የምንጠብቀው ፡ ተስፋችን ፡ ይክበርልን ፡ አምላካችን ፡ አሜን
|