From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ይባረክ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ያስተማረ
የጠላቴን ፡ ኃይል ፡ የሰበረ
ግራና ፡ ቀኜን ፡ ለይቼ ፡ የማላውቅ ፡ ብላቴና
ያልተፈተንኩኝ ፡ የውጊያውን ፡ ስልት ፡ ሳላውቀው ፡ ገና
ብርታትን ፡ ሰጥቶኝ ፡ ኃይሉን ፡ አልብሶኝ ፡ ጌታ ፡ ከሰማይ
ጐልያድን ፡ ጣልኩት ፡ ግንባሩን ፡ ብዬ ፡ በወንጭፍ ፡ ድንጋይ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ይባረክ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ያስተማረ
የጠላቴን ፡ ኃይል ፡ የሰበረ
ያልተገረዘ ፡ ፍልስጤማዊ ፡ ታሞኖ ፡ በጭኑ
እንዲሁ ፡ ሲፎክር ፡ ጌታ ፡ ቢያስነሳኝ ፡ ጠርቶ ፡ እኔኑ
በሳኦል ፡ ዐይን ፡ ፊት ፡ ያልተፈተንኩኝ ፡ የበግ ፡ ጠባቂ
ብመስልም ፡ እንኳን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ሆንኩለት ፡ በቂ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ይባረክ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ያስተማረ
የጠላቴን ፡ ኃይል ፡ የሰበረ
ጌታ ፡ ምስኪኑን ፡ ሰው ፡ ቢያደርገው ፡ አንስቶ ፡ ካፈር
ሳኦል ፡ ሺህ ፡ ዳዊት ፡ እልፍ ፡ ገደለ ፡ ተብሎ ፡ ቢጨፈር
ታዲያ ፡ በዚህ ፡ ላይ ፡ ምን ፡ ያስቆጣዋል ፡ ንጉሥ ፡ ሳኦልን
ማመስገን ፡ እንኪ ፡ ኃይል ፡ የሰጠኝን ፡ እግዚአብሔርን
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ይባረክ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ያስተማረ
የጠላቴን ፡ ኃይል ፡ የሰበረ
በክፉ ፡ መንፈስ ፡ ሃሳብ ፡ ተይዞ ፡ እኔን ፡ ሊገድለኝ
ና ፡ አስደስተኝ ፡ በገና ፡ ሞታ ፡ ብሎ ፡ ቢያታልለኝ
ጦሩን ፡ ወርውሮ ፡ ከግንቡ ፡ ጋራ ፡ ሊያጣብቀኝ
ቢያስብ ፡ እንኳ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈጥኖ ፡ ከእጁ ፡ አስጣለኝ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ይባረክ
ለእጆቼ ፡ ሰልፍን ፡ ያስተማረ
የጠላቴን ፡ ኃይል ፡ የሰበረ
|