እኛስ ፡ ተለይተናል (Egnas Teleyitenal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እኛስ ፡ ተለይተናል ፡ በኢየሱስ ፡ ተመርጠናል
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከሚሉት ፡ ሆነናል (፪x)

ቆርጠን ፡ ተነሥተናል ፡ ከጠፊዋ ፡ ዓለም
ከእሣት ፡ ባሕር ፡ ውስጥ ፡ ከሚዘገንን
በቃ ፡ ተለያየን ፡ ከጥፋት ፡ ጐዳና
ተመስገን ፡ ከሚሉት ፡ አንድ ፡ ሆነናልና

አዝ፦ እኛስ ፡ ተለይተናል ፡ በኢየሱስ ፡ ተመርጠናል
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከሚሉት ፡ ሆነናል (፪x)

አቤት! ደስታችን ፡ ሰላም ፡ እርካታችን!
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ስንል ፡ ለመሪያችን
በጣም ፡ ኅብረት ፡ አለን ፡ የእርሱ ፡ መሆናችን
ደስታን ፡ እንመሥርት ፡ በመለየታችን

አዝ፦ እኛስ ፡ ተለይተናል ፡ በኢየሱስ ፡ ተመርጠናል
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከሚሉት ፡ ሆነናል (፪x)

አሮጌ ፡ ቤት ፡ ፈርሶ ፡ አዲስ ፡ ቤት ፡ ገብተናል
የጥንቱ ፡ ኑሮያችንን ፡ ፈጽሞ ፡ ረስተናል
አሁን ፡ በአዲስ ፡ ሕይወት ፡ ጉዞ ፡ ጀምረናል
ይመስገን ፡ ለማለት ፡ ዕረፍት ፡ አግኝተናል

አዝ፦ እኛስ ፡ ተለይተናል ፡ በኢየሱስ ፡ ተመርጠናል
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ከሚሉት ፡ ሆነናል (፪x)