እኛ ፡ የምናምነው ፡ ግዑዝ ፡ አይደለም (Egna Yemenamnew Geuz Aydelem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዛሬ ፡ የምናየው ፡ ነገ ፡ ጠፊ ፡ ነው
ዛሬ ፡ የምንሰማው ፡ ነገ ፡ የሚቀር ፡ ነው
በዓለም ፡ ሚታየው ፡ ሁሉ ፡ አይኖርም
ጌታችን ፡ ብቻ ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘለዓለም

አዝ፦ እኛ ፡ የምናየው ፡ ግዑዝ ፡ አይደለም
በየምክንያቱ ፡ መልኩ ፡ አይቀየርም
ያው ፡ ነው ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ በዓለም

በጽኑ ፡ ድንጋይ ፡ የተገነባው
በዐይን ፡ ሲታይ ፡ ፈራሽ ፡ የማይመስለው
የምኖርበት ፡ የዚህ ፡ ምድር ፡ ቤት
እርሱም ፡ ይፈርሳል ፡ ቀን ፡ ሲደርስለት

አዝ፦ እኛ ፡ የምናየው ፡ ግዑዝ ፡ አይደለም
በየምክንያቱ ፡ መልኩ ፡ አይቀየርም
ያው ፡ ነው ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ በዓለም

እስኪ ፡ አስቡ ፡ ለትንሽ ፡ ሰዓት
በጣም ፡ ጠንካራ ፡ አለ ፡ የምትሉት
እርሱም ፡ ይቀልጣል ፡ ሲፈተን ፡ በእሳት
የማይቀር ፡ የለም ፡ በዚህ ፡ ዓለም

አዝ፦ እኛ ፡ የምናየው ፡ ግዑዝ ፡ አይደለም
በየምክንያቱ ፡ መልኩ ፡ አይቀየርም
ያው ፡ ነው ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ በዓለም

ተወዳዳሪ ፡ ያልተገኘለት
ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛ ፡ አባት
ልዩ ፡ ነውና ፡ አቻ ፡ የሌለው
ቅዱሳን ፡ ሁሉ ፡ ኑ ፡ እናክብረው

አዝ፦ እኛ ፡ የምናየው ፡ ግዑዝ ፡ አይደለም
በየምክንያቱ ፡ መልኩ ፡ አይቀየርም
ያው ፡ ነው ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ በዓለም

ከጥንት ፡ ነበርህ ፡ ምድርን ፡ መስርተህ
ሰማያትንም ፡ በእጅህ ፡ ዘረጋህ
ደግሞ ፡ እነዚህም ፡ ሁሉ ፡ ያረጃሉ
አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ በዘመን ፡ ሁሉ

አዝ፦ እኛ ፡ የምናየው ፡ ግዑዝ ፡ አይደለም
በየምክንያቱ ፡ መልኩ ፡ አይቀየርም
ያው ፡ ነው ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ በዓለም

የማይፈርሰውን ፡ የማያረጀውን
እኔ ፡ መርጫለሁ ፡ ያው ፡ እግዚአብሔርን
በምድር ፡ የሚታየው ፡ ሁሉ ፡ ይቀራል
እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጸንቶ ፡ ይኖራል

አዝ፦ እኛ ፡ የምናየው ፡ ግዑዝ ፡ አይደለም
በየምክንያቱ ፡ መልኩ ፡ አይቀየርም
ያው ፡ ነው ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ በዓለም