From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ዕዳችን ፡ ቀረ ፡ ድልም ፡ ተሰጠ
ዓመፃም ፡ ጠፋ ፡ ፅድቅም ፡ ተገኘ
የአምላክ ፡ ሕግ ፡ እንዳይረግመን
ክርስቶስ ፡ በሞቱ ፡ አዳነን
ሰው ፡ ሆይ ፡ ስማ ፣ እመን ፡ የምሥራችን
ክርስቶስ ፡ ሲሞት ፡ ተገዛን ፡ ሁላችን
ደሙ ፡ በመስቀል ፡ ከፈሰሰ
ዕዳችን ፡ ተደመሰሰ
ክርስቶስ ፡ ዋጀልን ፡ የፍርድ ፡ ነፃነት
ከኃጢአትም ፡ ቀንበር ፡ አርነት
ወደኔ ፡ ኑ ፡ ብሎ ፡ ያድናል
አማኝም ፡ ሁሉ ፡ ይድናል
ሰው ፡ ሆይ ፡ ስማ ፣ እመን ፡ የምሥራችን
ክርስቶስ ፡ ሲሞት ፡ ተገዛን ፡ ሁላችን
ደሙ ፡ በመስቀል ፡ ከፈሰሰ
ዕዳችን ፡ ተደመሰሰ
ልጆች ፡ ከሆነ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
በእርሱ ፡ አለነ ፡ የአምላክ ፡ ሞገስ
ኃይሉም ፡ ከውድቀት ፡ አድኖናል
ወደ ፡ ሰማይም ፡ ያደርሳል
ሰው ፡ ሆይ ፡ ስማ ፣ እመን ፡ የምሥራችን
ክርስቶስ ፡ ሲሞት ፡ ተገዛን ፡ ሁላችን
ደሙ ፡ በመስቀል ፡ ከፈሰሰ
ዕዳችን ፡ ተደመሰሰ
|