ዕዳ ፡ ተከፍሎ ፡ ድልም ፡ ተሰጠ (Eda Tekeflo Delem Tesete)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዕዳ ፡ ተከፍሎ ፡ ድልም ፡ ተሰጠ
መድኃኒታችን ፡ ሞተ ፡ ስለእኛ
ከኦሪት ፡ መርገም ፡ ከኃጢአት
ክርስቶስ ፡ አዳነን ፡ ሁላችን

አዝ፦ አሁን ፡ ሰው ፡ ሆይ! ይህን ፡ ነገር ፡ እመን
ክርስቶስ ፡ ሲሞት ፡ ተገዛን ፡ ሁላችን
አሁን ፡ ተቀበለውና ፡ ዳን
በደሙ ፡ ገዛን ፡ ሁላችን

አርነት ፡ ወጣን ፡ ፍርድ ፡ የለብንም
ሕሊናችንም ፡ ዓይነቅፈንም
ኑ! ወደ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ይላል
እርሱ ፡ አዳነን ፡ ሁላችን

አዝ፦ አሁን ፡ ሰው ፡ ሆይ! ይህን ፡ ነገር ፡ እመን
ክርስቶስ ፡ ሲሞት ፡ ተገዛን ፡ ሁላችን
አሁን ፡ ተቀበለውና ፡ ዳን
በደሙ ፡ ገዛን ፡ ሁላችን

ምንኛ ፡ ታላቅ ፡ የአምላክ ፡ ፀጋ
ልጆች ፡ ነነ ፡ የዓይኑ ፡ ብሌን
እንደዚህ ፡ ፍቅር ፡ ይገኛልን?
ክርስቶስ ፡ አዳነን ፡ ሁላችን

አዝ፦ አሁን ፡ ሰው ፡ ሆይ! ይህን ፡ ነገር ፡ እመን
ክርስቶስ ፡ ሲሞት ፡ ተገዛን ፡ ሁላችን
አሁን ፡ ተቀበለውና ፡ ዳን
በደሙ ፡ ገዛን ፡ ሁላችን