እጨነቃለሁኝ ፡ በችግር ፡ ኑሮዬ (Echeneqalehugn Becheger Nuroyie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እጨነቃለሁኝ
በችግር ፡ ኑሮዬ
ደስታህን ፡ ፍቅርህን
በላዬ ፡ አፍስሰው
ቶሎ ፡ እርዳኝ ፡ በፍቅር
ቀኑ ፡ ሳይደርስብኝ
ክቡር ፡ ፀጋህ ፡ ለከንቱ
እንዳልቀበለው

ተስፋዬ ፡ ሙሉ ፡ ነው
በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም
አይጨክንብኝም
የደከምሁኝ ፡ ልጁን
የከበደ ፡ ዕዳዬን
ተሸከመው ፡ በመስቀል
ስለዚህ ፡ እኖራለሁ
በይቅርታው ፡ ጽላ

እንዴት ፡ ልሆን ፡ ይሆን?
እርሱን ፡ ስተው ፡ ጊዜ
በዓለም ፡ ጨለማ
እቸገራለሁኝ
ወደኔ ፡ ግን ፡ ይመጣል
ብርሃን ፡ ሕይወትም ፡ ይዞ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ለመምራት
ለማውጣት ፡ ከሥቃይ