ደስታ ፡ ለዓለም (Desta Lealem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ደስታ ፡ ለዓለም ፡ ጌታ ፡ መጥቷል
ምድር ፡ ተቀበይው
ልባችሁን ፡ አዘጋጁ
ሰማይና ፡ ምድር ፡ ባንድነት ፡ ዘምሩ
መዝሙር ፡ መዝሙር ፡ ለህጻኑ

ደስታ ፡ ለዓለም ፡ አዳኝ ፡ ነግሷል
ሰዎች ፡ ዘምሩለት
የዓለም ፡ ሜዳ ፡ ተራራውም
ደስታውን ፡ ይናገር ፡ ምድርም ፡ ትሽበር
ምድር ፡ ምድርም ፡ ትሸበር

ኃጢአት ይጥፋ፡ ሐዘን ፡ ይራቅ
ምድርም ፡ ከሾህ ፡ ትረፍ
በረከቱን ፡ ሊያፈስ ፡ መጥቷል
መርገምንም ፡ ሊሽር (፪x)
መርገም ፡ መርገምንም ፡ ሊሽር

የዓለም ፡ ገዢ ፡ ጻድቅ ፡ ፈራጅ
ሕዝቡን ፡ ሊያገለግል
የክብሩ ፡ ኃይል የፅድቁንም ፡ ምንጭ
ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ወርዷል (፪x)
ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ወርዷል