ደስ ፡ ይበለን ፡ እንዘምር (Des Yebelen Enzemer)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ

መላዕክት ፡ ዘመሩለት ፡ ሰማይም ፡ ደመቀ
ኢየሱስ ፡ መወለዱ ፡ ለድሆች ፡ ታወቀ
መንፈስ ፡ የፀለለው ፡ የከበረ ፡ ሕፃን
መድኅን ፡ ተወለደ ፡ ከኃጢአት ፡ ሊያነፃን

አዝደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ

ድግሥ ፡ አዘጋጅቶ ፡ የሰማዩ ፡ ልዑል
በልጁ ፡ ጋበዘን ፡ ሃብታም ፡ ድሃ ፡ ሳይል
ዕውር ፡ ወይ ፡ ጐባጣ ፡ ሁሉም ፡ ይገባሉ
የዘለዓለም ፡ ሐሴት ፡ በእርሱ ፡ ይወርሳሉ

አዝደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ

ኢየሱስ ፡ በልባችን ፡ ዛሬ ፡ ተወለደ
ለእኛ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ እርሱን ፡ ለወደደ
ለተጠጋው ፡ ሁሉ ፡ መቸገሩን ፡ አይቶ
ዛሬም ፡ ይወለዳል ፡ አይተውም ፡ ሰል

አዝደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ