ደስ ፡ ይበለኝ ፡ ሃዘን ፡ ይራቅልኝ (Des Yebelegne Hazen Yeraqelegn)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ደስ ፡ ይበለኝ ፡ ሃዘን ፡ ይራቅልኝ
እግዚአብሔር ፡ ይወደኛል
አምላካችን ፡ አባት ፡ ከሆነልኝ
ስለ ፡ ልጁ ፡ እርሱ ፡ ያስባል
በየደቂቃው ፡ የደረሰኝን
አባቴ ፡ በፍቅሩ ፡ ልኮታል
ለየቀኑም ፡ የሚጠቅመኝን
ደስታም ፡ ኃዘንም ፡ ያካፍላል
ጩኸቴን ፡ ሊሰማ ፡ አይሰለችም
ሸክሜንም ፡ ያነሣልኛል
በድካሜ ፡ ከእኔ ፡ ዘንድ ፡ አይለይም
ስሙም ፡ መካር ፡ ኃያል ፡ ይባላል
ክቡር ፡ ገንዘቡ ፡ እንዳይጠፋበት
እርሱ ፡ ራሱ ፡ ይጠነቀቃል
እንደ ፡ ቀኑም ፡ ኃይሉ ፡ ሊሆንለት
ልጁን ፡ ፀጋው ፡ ያበረታዋል
አምላኬ ፡ እንዲህ ፡ ስታስብልኝ
እኔስ ፡ ሃሣቤን ፡ ልተው ፡ እርዳኝ
ዕምነቴን ፡ ከቃልህ ፡ ጨምርልኝ
በጅህም ፡ ወዳገሬ ፡ ምራኝ
ደስ ፡ ሲለኝ ፡ ስጨነቅም ፡ በሃዘን
አንተ ፡ ሁሉን ፡ እንደሰጠኸኝ
ተስፋህን ፡ ተቀብዬ ፡ ለማመን
ጌታ ፡ ሆይ! አንተ ፡ አስተምረኝ
|