ደስ ፡ እንዲለን ፡ ይገባናል (Des Indilen Yigebanal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ደስ ፡ እንዲለን ፡ ይገባናል
ባገኘነው ፡ ድንቅ ፡ ነገር
አምላክ ፡ አሁን ፡ ይምረናል
ፍርዳችን ፡ ሞት ፡ የነበር
ሊምረን ፡ እንደ ፡ ወደደ
የሚለን ፡ ቃሉን ፡ ሰደደ
ይህም ፡ ደስታችን ፡ ሆነ

የሰይጣን ፡ ባሪያ ፡ ነበርሁኝ
መዳኔም ፡ አልተቻለም
በኃጢአቴ ፡ ታሰርሁኝ
ልጠፋ ፡ ለዘለዓለም
ወደ ፡ ሲዖል ፡ እሣት ፡ ልወርድ
በገዛ ፡ ሕሊናዬ ፡ ፍርድ
እንደሚገባኝ ፡ ሆነ

ተስፋ ፡ ስቆርጥም ፡ ከጥፋት
መዳን ፡ ስላልታየልኝ
አምላክ ፡ በምሕረቱ ፡ ብዛት
በአባት ፡ ፍቅር ፡ አየኝ
በኃጢአቴ ፡ ታስሬ ፡ ሳለሁ
ተሰጠኝ ፡ የአባቴ
ቸርነትና ፡ ፍቅር

እንዲህ ፡ ብሎ ፡ ተናገረ
እራራላቸዋለሁ
እኒያን ፡ ምስኪን ፡ እሥሮች
ለልጄ ፡ እሰጣለሁ
በደሙ ፡ ከዘለዓለም ፡ ሞት
ሊያድናቸው ፡ አዘዝሁት
ሊሆንላቸውም ፡ ሕይወት

አባቴም ፡ እንደ ፡ ፈቀደ
ወልድ ፡ ታዘዘ ፡ በፍቅሩ
ከሰውም ፡ ሥጋ ፡ ተዋሐደ
ሲሰወርበት ፡ ክብሩ
ሕግ ፡ በእኔ ፡ እንደ ፡ ፈረደ
ሊሞት ፡ በመስቀል ፡ ወረደ
ከሞቴም ፡ ሊያወጣኝ

ከግቡ ፡ ፍርዴም ፡ እንድድን
ሕይወቴን ፡ ለወጠልኝ
የከበረም ፡ የኢየሱስ ፡ ደም
በመስቀል ፡ ፈሰሰልኝ
ሲሞት ፡ አወጣኝ ፡ ከፍርዴ
ሆነልኝም ፡ አማላጄ
ባባቱም ፡ ፊት ፡ ቆመልኝ

ከዚህም ፡ ዓለም ፡ መከራ
ወደ ፡ አባቱ ፡ ወጣልኝ
ለጭንቀቴም ፡ የሚራራ
ጰራቅሊጦስ ፡ መጣልኝ
ለንስሐ ፡ ይጠራኛል
በዕውነትም ፡ ይመራኛል
በልቤም ፡ አደረልኝ

ለአምላክ ፡ ውዳሴ ፡ ይሁን
ምሥጋናም ፡ ለዘለዓለም
ይህን ፡ ረድዔት ፡ ከሰጠነ
በአምላክ ፡ ተስፋ ፡ አለን
ኃጢአትና ፡ ሞት ፡ መርገምም
በክርስቶስ ፡ ሞት ፡ አስወገደ
ማን ፡ ነው ፡ የሚያስኮንነን?