ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (Des Des Yilegnal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. በጌታ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ በክንፉ፡ አድሬ
የእርሱን ፡ ድንቅ ፡ ሥራ ፡ አውርቼ ፡ መስክሬ
ልጨርስ ፡ ልፈጽም ፡ አቅቶኛልና
እንዲያው ፡ በዝማሬ ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ እግዚአብሔርን ፡ ስጠራ
በምስጋና ፡ ሆኜ ፡ ከልቤ
ፍቅሩን ፡ ምህረቱን ፡ አስቤ

2. ምንም ፡ አላደረኩም ፡ ምንም ፡ አልሰጠሁት
አምላኬ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ ዋጋም ፡ አልከፈልኩት
እንዲያው ፡ በጸጋው ፡ ኃይል ፡ ጠብቆኛልና
ለዚህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምስጋና (፪x)

አዝ፦ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ እግዚአብሔርን ፡ ስጠራ
በምስጋና ፡ ሆኜ ፡ ከልቤ
ፍቅሩን ፡ ምህረቱን ፡ አስቤ

3. ተስፋ ፡ እየቆረጥኩ ፡ ስወድቅ ፡ ስነሣ
ሸለቆ ፡ ገብቼ ፡ ውለታውን ፡ ስረሣ
ጌታ ፡ ይበርከኛል ፡ በፀጋው ፡ እንደገና
ሕያው ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ ልቅረብ ፡ በምስጋና

አዝ፦ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ እግዚአብሔርን ፡ ስጠራ
በምስጋና ፡ ሆኜ ፡ ከልቤ
ፍቅሩን ፡ ምህረቱን ፡ አስቤ

4. ምስጋና ፡ ሲያንሰው ፡ ነው ፡ ዝማሬውም ፡ ጭምር
በምስኪኑ ፡ ልጅ ፡ ውስጥ ፡ እንደዚህ ፡ ሲከበር
ታዲያ ፡ ምን ፡ ልክፈለው ፡ ለዚህ ፡ መድኃኒቴ
ዝማሬዬን ፡ ውሰድ ፡ ከዚች ፡ አንደበቴ (፪x)