ደስ ፡ ብሎናል ፡ በቤትህ (Des Belonal Bebieteh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search


1. ከጨለማ ፡ ያወጣኸን ፡ ክበርልን
ከእስራት ፡ የፈታኸን ፡ ክበርልን
ኑሮአችንን ፡ የለወጥኸው ፡ ክበርልን
ሁሉን ፡ መልካም ፡ ያደረከው ፡ ክበርልን

አዝ፦ ደስ ፡ ብሎናል ፡ በቤትህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆናችን ፡ ተስማምቶናል
ለዘለዓለም ፡ ክበርልን ፡ ንገሥልን (፪x)

2. አቤቱ ፡ ደስታችን ፡ ነህ ፡ ክበርልን
የብርሃን ፡ መንገዳችን ፡ ነህ ፡ ክበርልን
መመኪያ ፡ ኃይላችን ፡ ነህ ፡ ክበርልን
የሰላም ፡ መኖሪያችን ፡ ነህ ፡ ክበርልን

አዝ፦ ደስ ፡ ብሎናል ፡ በቤትህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆናችን ፡ ተስማምቶናል
ለዘለዓለም ፡ ክበርልን ፡ ንገሥልን (፪x)

3. ምህረትህ ፡ አላለቀም ፡ ክበርልን
ፍቅርህ ፡ አልተለወጠም ፡ ክበርልን
ዛሬም ፡ ታማኝ ፡ ጌታችን ፡ ክበርልን
ምስጢረኛዬ ፡ ወዳጃችን ፡ ክበርልን

አዝ፦ ደስ ፡ ብሎናል ፡ በቤትህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆናችን ፡ ተስማምቶናል
ለዘለዓለም ፡ ክበርልን ፡ ንገሥልን (፪x)

4. መልካም ፡ ኧረኛችን ፡ ነህ ፡ ክበርልን
ደስታ ፡ ሰላማችን ፡ ነህ ፡ ክበርልን
እጅግ ፡ ተስማማን ፡ ቤትህ ፡ ክበርልን
ፍቅርህ ፡ አባትነትህ ፡ ክበርልን

አዝ፦ ደስ ፡ ብሎናል ፡ በቤትህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆናችን ፡ ተስማምቶናል
ለዘለዓለም ፡ ክበርልን ፡ ንገሥልን (፪x)