ድምጽህ ፡ ይሰማኝ (Demtseh Yisemagn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. እኔ ፡ ያንተ ፡ በግ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ እረኛ
ከመንጋህ ፡ ኮብልዬ ፡ ብሆን ፡ እልከኛ
የምድረበዳ ፡ ኑሮ ፡ እንደማይመች ፡ አውቃለሁና
ሰብስበኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻዬን ፡ ነኝና
አደራህን ፡ ጌታ

አዝድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ (፪x)
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ
መመሪያ ፡ እንዲሆነኝ
ከክፉም ፡ እንዲጠብቀኝ
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ ፡ ድምጽህ ፡ ይሰማኝ

2. መስሎኝ ፡ ነበር ፡ ያኔ ፡ በግል ፡ የምገፋው
ከቤትህ ፡ ወጥቼ ፡ መሞተን ፡ ሳላውቀው
ያ ፡ ትምክህቴ ፡ ሁሉ ፡ አሁን ፡ ከነ ፡ ዘንድ ፡ የለምና
መባዘን ፡ በቃኝ ፡ ሰልችቶኛልና
አደራህን ፡ ጌታ

አዝድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ (፪x)
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ
መመሪያ ፡ እንዲሆነኝ
ከክፉም ፡ እንዲጠብቀኝ
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ ፡ ድምጽህ ፡ ይሰማኝ

3. ምንም ፡ አላተረፍኩ ፡ ከቤትህ ፡ ወጥቼ
ያለኝን ፡ ከመክሰር ፡ ለዓለም ፡ ሰጥቼ
ይህች ፡ አጭር ፡ ዘመኔ ፡ እንደ ፡ ጥላ ፡ ከኔ ፡ ላይ ፡ ሳታልፍ
ስትጠራኝ ፡ ልሰማ ፡ በቅንድህ ፡ ላይ ፡ ልረፍ
አደራህን ፡ ጌታ

አዝድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ (፪x)
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ
መመሪያ ፡ እንዲሆነኝ
ከክፉም ፡ እንዲጠብቀኝ
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ ፡ ድምጽህ ፡ ይሰማኝ

4. አውቄያለሁ ፡ አሁን ፡ ነፍሴ ፡ እንደተጐዳች
ወደ ፡ ሞትም ፡ ማጀት ፡ ቁልቁል ፡ እንደሮጠች
መቅበዝበዜ ፡ ታይቶት ፡ መንፈስህ ፡ በኔ ፡ እጅግ ፡ አዝኗልና
ወደ ፡ እረፍት ፡ መግባት ፡ ናፍቄአለሁና
አደራህን ፡ ጌታ

አዝድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ (፪x)
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ
መመሪያ ፡ እንዲሆነኝ
ከክፉም ፡ እንዲጠብቀኝ
ድምጽህ ፡ ይሰማኝ ፡ ለኔ ፡ ድምጽህ ፡ ይሰማኝ