ደመናም ፡ የለም ፡ የጠራ ፡ ሠማይ ፡ ነው (Demenam Yelem Yetera Semay New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ብዙ ፡ ደከምኩኝ ፡ አልተሳካም
ብዙም ፡ እሮጥኩኝ ፡ ግን ፡ አልሆነም
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ አላማ ፡ አለህ
ሁሉን ፡ በጊዜው ፡ ታደርጋለህ (፪x)

አዝ፦ ደመናም ፡ የለም ፡ የጠራ ፡ ሠማይ ፡ ነው
ነፋስም ፡ የለም ፡ ምልክት ፡ የማየው
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ዝናብን ፡ ከላይ ፡ ታዘንባለህ
አንተ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ሸለቆውን ፡ ውኃ ትሞላለህ

2. አምናለሁ ፡ ጌታ ፡ አትረሳኝም
የልቤ ፡ መሻት ፡ ቢዘገይም
በአንተስ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም
ቃልህን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትለውጥም (፪x)

አዝ፦ ደመናም ፡ የለም ፡ የጠራ ፡ ሠማይ ፡ ነው
ነፋስም ፡ የለም ፡ ምልክት ፡ የማየው
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ዝናብን ፡ ከላይ ፡ ታዘንባለህ
አንተ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ሸለቆውን ፡ ውኃ ትሞላለህ

3. በአንተ ፡ ማረፉ ፡ ይበጀኛል
በከንቱ ፡ ብደክም ፡ ምን ፡ ይገኛል
አንተን ፡ ልጠብቅህ ፡ ይሻለኛል
የእኔውስ ፡ መንገድ ፡ ያጠፋኛል (፪x)

አዝ፦ ደመናም ፡ የለም ፡ የጠራ ፡ ሠማይ ፡ ነው
ነፋስም ፡ የለም ፡ ምልክት ፡ የማየው
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ዝናብን ፡ ከላይ ፡ ታዘንባለህ
አንተ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ
ሸለቆውን ፡ ውኃ ትሞላለህ