ድል ፡ ነሥተሃል ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ (Del Nestehal O Eyesus)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ድል ፡ ነሥተሃል ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ !
ዕርቃችን ፡ አንተ ፡ ነህ
ለአንተ ፡ ለሕይወት ፡ ንጉሥ
ምሥጋና ፡ እንስጥህ
የሞትን ፡ ኃይል ፡ ከሰበርክ
ለእኛ ፡ ሕይወት ፡ ፈጥርክ
በቅዱስ ፡ ትንሣዔህ

መሬቱ ፡ ቤትህ ፡ ነበር
ለእኛም ፡ ይከፈታል
እኛንም ፡ ከመቃብር
ድምጽህ ፡ ያስነሣናል
አንተንም ፡ በሕይወቱ
የወደደህ ፡ በሞቱ
በዕቅፍህ ፡ ውስጥ ፡ ያርፋል

ኋለኛውም ፡ ቀን ፡ ሲነጋ
በግርማህ ፡ ስትታይ
ዙፋንህ ፡ ሲዘረጋ
ለፍርድ ፡ በአሕዛብ ፡ ላይ
መለከቱም ፡ ሲሰማ
ሕይወቱ ፡ እንደለማ
ድምጽህ ፡ ያስታውቃል